የታክሲ (Cab) ደህንነት ለጎብኚዎች

Written by  Sunday, 05 July 2015 07:13
Rate this item
(1 Vote)

የታክሲ (Cab) ደህንነት ለጎብኚዎች

በማንኛውም ሰዓት ወደ ታክሲ ወይም በሊሎች መጓጓዣ  ውስጥ ስንገባ በተወሰነ መልኩ ራሳችንን ለሌላ ሰው እጅ ኣሳልፈን እንደመስጠት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ የማናውቀው ሰው ነው የሚያሽከረክረው፡፡ ስለሆነም በታክሲም ሆነ በሊላ መጉዋጉዋዣ በሚዘዋወርሩበት ጊዜ ስለ ደህንነትዎ በጥንቃቄ ማሰብ አለብዎት፡፡

አብዛኞቹ የታክሲ ሹፌሮች ስላሉበት ከተማ  ሪስቶራንቶች፣ መዝናኛዎች፣ እና የመሳሰሉት በቂ መረጃ አላቸው፡፡ የታክሲ ሹፌሮች አደገኛና ሰላም የሆኑትን ሰፈሮች እንዲሁም ያረፉበት ሆቴል ምን ዓይነት ችግር እንዳለበት ወይም ምን ሊያጋጥምዎት እንደሚችል ያውቃሉ ተብሎ ይገምታል፡፡ ስለዚህ አብዘኞቹ ሹፌሮች ተግባቢዎች በመሆናቸው ከእነርሱ ጋር ማውራት መረጃ ለመሰብሰብ ፡ ቋንቋን ለመለማመድ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ቢሆንም ስለ ራስዎ ብዙ መረጃ ከመስጠት ይቆጠቡ፡፡ ምክንያቱም ይህንን መረጃ ለሌላ ሰው አሳልፈው ከሰጡ አደጋ ሊያጋጥምዎትም ይችል ይሆናል፡፡

ስለ ታክሲ ደህንነት ከባለሙያዎች የተሰጡትን 10 ዝርዝሮች ይመልከቱ፡-

ስለክፍያው ሁኔታና ስለቲፕ (ጉርሻ)መጠየቅ

ያረፉበት ሆቴል ሰራተኞች ወይም አስጎብኚዎ መሄድ ወደፈለጉበት ቦታ ታክሲ እስከነቲፑ ምን ያህል እንደሚያስከፍል ሊነግሮዎት ይችላሉ፡፡ ክፍያውን ቀድመው ካወቁ ከታክሲ ሹፌሩ ጋር መንገድ ከመጀመርዎ በፊት ይነጋገሩ ጊዜ ይቆጥባል ጭቅጭቅንም ያስቀራል፡፡

 

ታክሲን መንገድ ላይ ቆሞ ከመፈለግ ይልቅ ደውለው ይጥሩ

አንዳንድ የታክሲ ሹፌሮች ከዘራፊዎች ጋር በትብብር ይሰራሉ ይባላል። አካሄዳቸውም እንደዚህ ነው፡፡ ሹፌሩ ደህና የሚባል እቃ ማለትም እንደ ጌጣጌጥ፣ ካሜራ ወይም ሞባይል ካየ በስልክ መልእክት ለሌባው ይልካል፡፡ ሌባው ታክሲውንና የሚሄድበትን መንገድ ስለሚያውቅ የመንገድ መብራት ያለበትና ታክሲው የሚቆምበት ጋር ይጠብቀዋል፡፡ ታክሲው ሲቆም በፍጥነት በሩን ከፍቶ እቃዎትን ይዞ ይሰወራል፡፡

ታክሲ ደውለው በሚያስመጡበት ጊዜ ግን የመኪናውን ቁጥር ይጠይቁ በትክክል አይተውም የድርጅቱ ስምና ስልክ ቁጥር ታክሲው ላይ እንዳለ አይተው አረጋግጠው ይግቡ፡፡

 

ጠጥተው ከሆነ ብቻዎን በታክሲ አይሂዱ

መጠጥ ጠጥተው ከሆነ በታክሲ መሄድ ይመረጣል ። ነገር ግን ብቻዎን ሳይሆን ከሌላ ሰው ጋር መሆን አለበት፡፡ መጠጥ ጠጥተው ታክሲ ውስጥ ገብተው መንገድ በሚጀምሩ ሰዓት እንቅልፍ ሊወስድዎት ይችላል፡፡ እንዲሁም በስካር ነገሮችን በንቃት ለመከታተል ስለሚያስቸግር እራስዎን ከታክሲ ሹፌር ወይም ከሌላ ሰው ጥቃት መጠበቅ አይችሉም፡፡ ብዙዎች በስካር መንፈስ ታክሲ ውስጥ ገብተው ተደፍረዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተዘርፈዋል አልፎም ተርፎም ተገድለዋል፡፡

መጠጥ ጠጥተው በታክሲ የሚሄዱ ከሆነ ያልጠጣ ጓደኛዎን ይዘው እንቅልፍ ሳይተኙ ይጉዋዙ።

 

ሬድዮ፣ ሜትር፣መታወቂያ መኖሩን ማረጋገጥ

ሁሉም ህጋዊና ፍቃድ ያላቸው ታክሲዎች፡- ለአከፋፈል እንዲመች የተጓዙበትን መንገድ የሚለካ ሜትር፣ ከድርጅታቸው ጋር የሚገናኙበት ራድዮ፣ የታክሲ ሹፌሩ ደግሞ ማንነቱን የሚገልፅ ህጋዊ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ወደ ታክሲ በሚመጡበት ጊዜ እነዚህ ነገሮች ካላዩ አይሳፈሩ፡፡ ገብተው ከመቀመጥዎ ቢፊት በሮቹ በደንብ እንደሚሰሩ ያረጋግጡ ምክንያቱም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ጎብኚዎችን በዚህ መልኩ ስለሚያፍኑ፡፡

ከኋላ ይቀመጡ

በኋላ መቀመጫ ላይ በሚቀመጡ ሰዓት ከሹፌሩም ሆነ ከሚያልፉ ሰዎች ጥቃት ይርቃሉ፡፡ ቀረብ ብሎ መቀመጥ ለአደጋ ተጋላጭ ስለሚያደርገን በኋለኛው መቀመጫ ላይ መቀመጥ ይመረጣል፡፡

በሚጉዋዙበት ሰዓት የማቅለሽለሽ ህመም ከተሰማዎት ምናልባት ከታክሲው ውስጥ በመነጨ ሽታ መሆን ኣለመሆኑን ያረጋግጡ። ኣንዳንዶች ጢናን የሚያውኩና የሚያፈዙ መድሀኒቶችን ይረጫሉና። ያለዚያም በኣየር ለውጥ ወይም በራስዎ የውስጥ ችግር መሆኑን ከተረዱ መድሀኒትዎን ይጠቀሙ፡፡

 

ሻንጣዎችዎን አጠገብዎ በማድረግ ውድ የሆኑ እቃዎችን ከእይታ ይደብቁ

ስለ አንዳንድ የሞባይል ቀፎዎች ያልዎት አመለካከት አናሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ባደጉት ሀገራት ስማርት ስልኮችን ለመስረቅ ቀላል ነው፡፡

ታክሲ በሚጠብቁበት ወቅት ወይም የመንገድ መብራት ላይ ሞባይል እየተጠቀሙ ከሆነ በዘራፊዎች እይታ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ማወቅ አለብዎት፡፡ አብዛኞቹ ሌቦች በተለይ የመንገድ መብራት ባለበት ቦታ ላይ ስልክ ነጥቆ ለመሮጥ 20 ሰከንድ በቂያቸው ነው፡፡ ስለዚህ የሞባይል ስልክዎንና ካሜራዎን ቦርሳዎት ውስጥ ከተው ቦርሳዎን በመዝጋት የእጅ ቦርሳዎትን፣ የሚታዘል ቦርሳዎትንና ሌሎች ቦርሳዎችዎን አጠገብዎ  በተለይ ከእግርዎ ስር ማስቀመጥ ይመረጣል፡፡ በመጨረሻ ከታክሲው በሚወርዱበት ሰዓት እግርዎን እንዳይጠልፍዎ ቅድሚያ ቦርሳዎን በማንሳት ይውረዱ፡፡

 

በቅድሚያ የት እንደሚሄዱ ማወቅ

መንገድ ከመጀመርዎ በፊት የት እንደሚሄዱ ምን ያህል ሰዓት እንደሚፈጅብዎትና ስለሚሄዱበት ቦታ መረጃ በደንብ ቢኖርዎት ይመረጣል፡፡ ሹፌሩ በማይሆን ወይም በተሳሳተ መንገድ ከወሰደዎት የኣካባቢው ሁኒታ ለእርስዎ ኣመቺ መሆኑን ኣረጋግጠው በአስቸኳይ ከታክሲው ይውረዱ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ወደ ቅርብ ሰው ወይም ለፖሊስ በመደወል ሁኒታዎን እንዲከታተሉ  ያድርጉ።

 

መስኮቶችን ዘግተው ይጓዙ

ሌቦች ጎብኝዎችን ለመስረቅ አመቺ ሁኔታ ካላጋጠማቸው ወደ ሌላ የተመቻቸ ቦታ ይሄዳሉ፡፡ ጎብኝዎች ቀላል በሆኑ ነገሮች ይጠቃሉ። ለምሳሌ መስኮት መዝጋት ቀላል ነው ፡ ከሌባው አንጻር ግን መስኮት ክፍት ከሆነለት ታክሲው በቆመበት ቅጽበት እቃ ቀምቶ ለመሮጥ ይመቸዋል። ሌላው ቀርቶ ያልተቆለፈ በር ከፍተው እቃ ይዘው ይሰወራሉ፡፡ አብዛኛው ሰው ንጹህ አየር ለማግኘት ነው መስኮት የሚከፍተው ፡ መከፈት ካለበት ደግሞ በትንሹ ሆኖ የመንገድ መብራት በሌለበትና መኪናው በዝግታ እንዲሂድ በማይገደድበት ቦታ ቢሆን ይመረጣል፡፡

 

የወቅቱን የገንዘብ ምንዛሬ ይወቁት

በአንዳንድ ሀገሮች የገንዘብ ምንዛሬ በየጊዜው ይለዋወጣል፡፡ አንዳንድ ሼፌሮች ሊያጨበረብርዎትና የማይረባ መልስ ሊሰጥዎት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የቦታውን ገንዘቦች በደንብ በማጥናት ምን ያህል መክፈል እንዳብዎት ጠንቅቀው ይወቁ፡፡ እርግጠኛ ካልሆኑ ከአስተናጋጅዎ ወይም ካረፉበት ሆቴል ሰራተኞች መረጃ ይጠይቁ፡፡

 

በአደጋ ጊዜ ማን ጋር መደወል እንደላብዎት ይወቁ

በውጭ ሀገር ከሆነ ያሉት ያሉበትን ሀገር የአደጋ ጊዜ መደወያ ስልክ ይያዙ፡፡ ለዚህ ነው ስልክዎን ከእይታ ሰውረው መያዝ ያለብዎት ፡ ሌላው ነገር ታክሲ ውስጥ የመንገደኞች መቀመጫ ላይ ሰው ካለ ምንም ዓይነት ምክንያት ቢኖርም እንዲወርድ ያድርጉ። ኣንድ ታክሲ ለኣንድ ሰው በሚለው መርህ መሰረት እርስዎ ወይም ከእርስዎ ጋር ካለ ፡ እርስዎ ማንነቱን ኣውቀው ከፈቀዱለት ሰው በቀር ሊላ ሰው ሊሳፈር ኣይችልም።ይህ ካልሆነ ግን ለእርስዎ ጥሩ ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ አብዘኛውን ጊዜ ሰዎች የስርቆት፣ የመታፈን፣ መደፈርና ግድያ አደጋ የሚጋጥማቸው በእንደዚህ ያለ ምክንያት ነው፡፡ የዋህነትዎ በማያውቁት ሀገር ፡ ባህልና ህዝብ መካከል መሆን የለበትም።

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Travel safety የታክሲ (Cab) ደህንነት ለጎብኚዎች