ጉብኝት (ጉዞ)

Written by  Monday, 20 April 2015 02:00
Rate this item
(0 votes)

ጉብኝት (ጉዞ)

 

ጉዞዎ ከተሟላ ጤንነት ጋር እንዲሆን የሚከተሉትን ነጥቦች አቅርበናል

ዓለምን ዞሮ ማየት ደስ የሚል አጋጣሚ ነው፡፡ ቤተሰብዎን ለመጠየቅም ይሁን ጓደኛዎን ለማየት ወይም በስራ ጉዳይም ሆነ በትምህርት አለበለዚያም ለሽርሽር ጉዞ በሚያደርጉበት ሰዓት ፡ ከቢትዎ ከመውጣትዎ በፊት ማድረግ ያለብዎት አንዳንድ ነገሮች እንንገርዎ (እናስታውስዎ)፡-

እድሜዎ 16ም ሆነ 60 ከመጓዝዎ በፊት የጉዞ ዕቅድ ማውጣት አለብዎት፡፡ እቅድ ማውጣት ካልተጠበቀ ችግርና ከዚህም በላይ በጉዞ ወቅት ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች ላለመያዝ ይረዳናል፡፡

ታዋቂ (sun - seeker) የሆኑ ቦታዎችም ላይ ቢሆን አደገኛ የሆኑ ተላላፊ በሽታዎች ስለሚኖሩ ራስዎትን ይጠብቁ፡፡ አብዛኞቹ ቦታዎች በጉዞ ላይ ለሚያጋጥሙ ህመሞች ውጤታማ የሆነ protective measures አላቸው፡፡ ይህ ዓምድ የተዘጋጀው የጉብኝት ወይም የጉዞ ጊዜዎን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ነው፡፡ የጉዞዎን ዕቅድ ከማውጣት ጀምሮ እስከሚመለሱ ድረስ ያለውን የጉዞ ሁኔታ ጠቃሚ ሀሳቦችን ያገኛሉ፡፡ ምክንያቱም የጉዞ ዋናው ዓላማ አስደሳች ጊዜን በማሳለፍ የማይረሱ ትዝታዎችን ማፍራት ነውና፡፡

 

የጉዞ ዕቅድ የማውጣት ጥቅም 

የተላላፊ በሽታዎች መከላከል የሚጀምረው ከቢትዎ ከመውጣትዎ በፊት ነው፡፡ የሁሉም ተጓዥ ዓላማ ጉዞውን በጤንነት ማጠናቀቅ ነው፡፡ ስለሆነም ቀደም ብለው ሊጎበኟቸው ስላሰቧቸው ቦታዎች መረጃ ያጣሩ ምክንያቱም ጉዞዎን ሳይታመሙ በነፃነት ለማድረግ፡፡

 

በሚጎበኟቸው ቦታዎች ለጤንነት አስጊ የሆኑ ነገሮችን እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ?

የውሃው ጥራት እንዴት ነው? ለመጠጥ ይሆናል ወይ?

ያረፉበት ክፍልና ምግቡ አገርዎ ካለው ምግብ ጋር ተመጣጣኝ ነው

በጉዞ ወቅት እንዳልታመም ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?

ያረፍኩበት ቦታ ላይ የተለየ ተላላፊ በሽታ በተከታታይ ያጋጥማል ወይ?

 

ጉዞዎንና የጉዞ እቅድዎን የሚረዳ ምንጭ

ለጉዞዎ እቅድ ማውጣት አሰልቺ ቢሆንብዎትም ተስፋ አይቁረጡ፡፡ ከታች በዝርዝር የቀረበው ፅሑፍ የሚፈልጉትን መረጃ ለማግኘት ስለሚረዳዎ ጉዞዎ አስደሳችና የተሳካ ይሆንልዎታል፡፡

አስጎብኚ ድርጅቶች ብዙ የሚጎበኙ ቦታዎች መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቲርና አለም አቀፍ ንግድ ግዜውን የጠበቀ የጉዞ መረጃ ያቀርባሉ ማስጠንቀቅያዎችና ወደ ውጭ አገር የሚሄዱ ተጓዦችን ስለሚሄዱበት ሀገር ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማቅረብ፣ ጎብኚዎች የደህንነት ስጋቶች የሆኑ ነገሮችን እንዲገነዘቡ ማድረግ፣ አደገኛ የአየር ሁኔታ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ የጤና ጉዳዮችና ስለፖለቲካ አለመረጋጋት።

የህዝብ ጤና ተቋማት የህብረተቡን ጤንነት  ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ይጠብቃሉ፡፡  ስለሆነም ይህ ድረ ገጽ በጉዞ ወቅት መወሰድ ያለበት የጤና ጥንቃቄ፣ የአደጋ ጊዜ ዝግጅት፣ ተላላፊ በሽታዎች፣ ጉዳትን ስለመከላከል በዝርዝር ያቀርባል፡፡

ይህ በጉዞ ወቅት መደረግ ስላለበት የጤና ጥንቃቄዎች የተሟላ መረጃ ይሰጣል፡ መዳረሻዎችን ጨምሮ ስለ በሽታዎችና ክትባት እንዲሁም ማስጠንቀቂያ።

የዓለም የጤና ድርጅት የተባበሩት መንግስታት የጤና ወኪል ነው፡፡ እዚህ ጤናን በተመለከተ የተለያዩ ጹሁፎችን ያገኛሉ፡፡ የአንድ ሀገር ዝርዝር መረጃና ስለ ወቅታዊ ዓለም አቀፍ በሽታዎች የተብራራ መረጃ ኣላቸው።

 

ክትባት እና በጉዞ ወቅት የሚያጋጥም በሽታ

ክትባት በሚወስዱ ሰዓት የሰውነትዎ በሽታውን የመከላከል አቅሙ ይጨምራል፡፡ በክትባት ምክንያት ገዳይ የሆኑ በሽታዎች  እንዲጠፋ ሆነዋል፡፡  ለምሳሌ እንደ ፈንጣጣ አሁን ደግሞ ፖሊዮንና ኩፍኝን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እየተሰራ ነው፡፡

በሚከተቡ ሰዓት የጤና ጥበቃ ሙያተኞች እንደሚያዙት እስከ መጨረሻው መከታተል አለብን፡፡ ነገር ግን በአለቀ ሰዓት ወስነው እንደሚጓዙት ከሆኑ ፈጣን ክታቦቶች ስላሉ መመሪያቸውን በመከተል መጠቀም ይቻላል፡፡

 

ክትባት እና በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ በሽታዎች

ሁለት ዓይነት የጉበት ቫይረሶች አሉ እነሱም Hepatitis A እና Hepatitis B ናቸው፡፡ በተጓዦች ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉም  ናቸው። ከዚህ በታች ያለው ጽሁፍ ስለነዚህ የጉበት በሽታዎችና ራሳችንን ከነዚህ በሽታዎች እንዴት መከላከል እንዳለብን ጠቃሚ መረጃ የያዙ ሲሆን በጠቅላላው ተጓዦች ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ሌሎች በሽታዎች ቢጫ ወባና በእብድ ውሻ መነከስን ጨምሮ ያብራራል፡፡

 

ጉበት ሀ (Hepatitis A)

Hepatitis A ለተጓዦች ክትባቱ በቀላሉ ይገኛል፡፡ Hepatitis A ከባድ የጉበት በሽታ ሲሆን ከሰውነት ከሚወጡ ቆሻሻዎች ጋር የተነካካ ምግብ ወይም መጠጥ በመጠጣት ነው የሚመጣው፡፡ በተበከለ ውሃ ውስጥ መዋኘትና የመሳሰሉትም በበሽታው ለመያዝ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 50% የሚሆኑት በበሽታው የታያዙት ሰዎች መንስኤውን አያውቁም፡፡ በHepatitis A የተያዘ ሰው ህመሙ ቀላል አይደለም ከ4 – 10 ሳምታት የአልጋ ቁራኛ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እስከ 6 ወር ወይም ከዚያም በላይ ሊቆይ ይችላል፡፡ ጉበት በሽታ የያዘው ሰው የህመሙ ምልክት ሳይታይበት በሽታውን ወደሌላ ሰው ሊያስተላልፍም  ይችላል እርሱም ለቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ የስራ ባልደረቦች ያዳርሳል።

 

ጉበት ለ (Hepatitis B)

 Hepatitis B ሌላኛው ከባድ የጉበት በሽታ ሲሆን ከሰውነት በሚወጡ ፈሳሾች ወይም ደም ይተላለፋል፡፡ በግብረስጋ ግኑኝነት፣ በጥርስ ህክምና፣ በንቅሳት፣ በአደጋ፣ ለተጎጂዎች የመጀመረያ እርዳታ በሚሰጡ ሰዓትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አስቡበት እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉና፡፡

 ከ 10% በላይ የሆኑ በHepatitis B የተያዙ አዋቂዎች በህይወት ዘመናቸው የቫይረሱ ተሸካሚዎች ይሆናሉ፡፡ ይህ ማለት በሽታውን ለሌሎች ያስተላልፋሉ ማለት ነው ምንም እንኳ የመታመም ምልክት ባያሳዩም፡፡ ከጊዜ በኋላ ስር በመስደድ አደገኛ የሆነ የጉበት በሽታ እንደ የጉበት ካንሰርና የመሳሰሉትን ያስከትላል፡፡

 

Hepatitis A and B የመያዝ አደጋዎች

 Hepatitis A and B በሽታ ክትባቱ ለተጓዦች በቀላሉ የሚገኝ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ክትባት በሽታን ለመከላከል የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ ምክንያቱም በሽታው የት እንዳለ ለማወቅ ስለሚከብድ ከየትኛውም ቦታ ሊይዝዎት ስለሚችል ነው፡፡

 

የበሽታውን አደጋዎች ቀድሞ ማወቅ የሚያስከትለውን ችግር ያስቀራል

Hepatitis A በሽታን የሚያመጡ ዝርዝሮች፡-

በተበከለ ውሃ ውስጥ መዋኘት፡

በታመመ ሰው የተዘጋጀ ምግም መመገብ፡

ለአደጋ የሚያጋልጡ ምግቦችን መመገብ እንደ ሰላጣና የመሳሰሉት፡

በበሽታው ከታያዙ የሀገሬው ሰዎች ጋር መገኛኘት፡

የተለመዱና ጎብኚዎች ከሚጎበኟቸው ቦታዎች ውጪ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ፡ 

 

Hepatitis B በሽታን የሚያመጡ ዝርዝሮች፡-

በአደጋ ምክንያትም ሆነ በሌላ ሜዲካል ህክምናና የጥርስ ህክምና።

ለተጎዱ ሰዎች የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ መስጠት፡

ንቅሳት መነቀስ፣ በጩቤ መወጋትና የመሳሰሉት።

በጉብኝት ወቅት ያልታቀደ የግብረስጋ ግኑኝነት።

 

 ክትባት ለሁሉም ተጓዦች አይስማም፡ አንዳንድ  ጊዜ ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለሆነም ምን ዓይነት አማራጭ መጠቀም እንዳለብን የህክምና ባለሙያዎችን ወይም የጤና ተቋም ሄደው ያረጋግጡ፡፡

በ 2000 ዓ.ም የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው 74% የሚሆኑ ተጓዦች በHepatitis B የመያዝ ከባድ አደጋ ውስጥ ነበሩ፡፡ ስለሆነም ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ክትባቱን መውሰድ ጥሩ ውሳኔ ነው፡፡

 

 

 በየዓመቱ ብዙ ሰዎች ወደ ካሪብያንና የመሳሰሉት ይጓዛሉ፡፡ ግን Hepatitis A ወይም B ሊይዛቸው እንደሚችል ግን አያውቁም፡፡

 ረዘም ያለ ጉዞ በሚያቅዱበት ሰዓት ሊያስታውሱ የሚገባዎት ነገር እያንዳንዷ ቀን እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ጊዜ በHepatitis A ወይም B የመያዝ እድልዎ ሰፊ መሆኑን ነው፡፡ ደረጃውን የጠበቀ የእንግዳ ማረፍያ ውስጥም ቢያርፉ እንኩዋን ኣሁንም እድሉ አለ፡፡ አብዛኞች ተጓዦች በጉበት በሽታ ሲያዙ የተያዙበትን ምክንያት አያውቁም፡፡ አንዴ ከተያዙ መታመማቸውን እንኳ ሳያውቁ ለሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡

 እነዚህ በሽታዎች አሉበት ተብለው ከሚገመቱ ቦታዎች ላይ ጉዞ የሚያደርጉ ሁሉ ቀድመው ክትባቱን እንዲወስዱ ይመከራል፡፡

 ጥሩ ዜና Hepatitis A and B ሊከላከልልን የሚችል ክትባት መኖሩ ነው፡፡ Twinrix® ክትባት ደግሞ ሁለቱንም ለመከላከል ይረዳናል፡፡

 ምንም ዓይነት ጉዞ ሲያስቡ በተለይ ረዘም ያለ ለምሳሌ ወደ እነ ካሪብያን ኣፍሪካ ዓይነት ቦታዎች ከሆነ የህክምና ባለሙያ ሳያማክሩ ወይም ወደጤና ተቋም ሳይሄዱ እቅድዎን አይጨርሱ፡፡

 

በአጠቃላይ በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ በሽታዎች

የእብድ ውሻ ንክሻ የሚያስከትለው በሽታ (RABIES)

ራቢስ (RABIES) አደገኛ የቫይረስ በሽታ ሲሆን በሰፊው የቤትና የዱር አጥቢ እንስሳቶችን ያጠቃልላል። የለሊት ወፍን ጨምሮ፡፡ ይህ በሽታ በአብዛኛው አገር የሚከሰት በሽታ ነው፡፡

አብዛኞቹ መንገደኞች በቫይረሱ በተበከለ እንስሳት ስለሚነከሱ በበሽታው ይያዛሉ፡፡  አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በመንገድ ላይ ውሻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ ክትባቱ አስፈላጊ ነው ጉዞዎ በበሽታው በተያዙ እንስሳቶች ባሉበት የሚሆን ከሆነ፡፡

 

ቢጫ ወባ (YELLOWFEVER 

ቢጫ ወባ የቫይረስ በሽታ ሲሆን በበሽታው በያተዘ ትንኝ ምክንያት ወደ ሰው ይተላለፋል፡፡ በሽታው በአፍሪካ ከሰሀራ በታች፣ በትሮፒካል ደቡብ አሜሪካ ብቻ ነው የሚገኘው፡፡ ስለዚህ ለአብዛኞች ተጓዦች ቢጫ ወባ የሚያሰጋቸው አይደለም፡፡ ቢሆንም ጉዞዎት ቢጫ ወባ ያለባቸውን ቦታዎች የሚጨምር ከሆነ በበሽታው የመያዝ አደጋ ላይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

 

ታይፎይድ (TYPHOID FEVER)

ታይፎይድ በባክቴሪያ የሚመጣ ህመም ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ሰውነት በሚወጣ ቆሻሻ የተነካካ ምግብ ወይም መጠጥ የበላና የጠጣ ሰው በበሽታው ይያዛል፡፡ ለምሳሌ በበሽታው የተያዘ ሰው እጁን ሳይታጠብ ምግብ ቢያዘጋጅ በሽታው ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ንጽህናቸው ያልተሟላና በማደግ ላይ ወዳሉ ሀገሮች ጉዞ ለማድረግ ካሰቡ በታይፎይድ የመያዝ እድልዎ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ከባድ ጥንቃቄ በመውሰድ ክትባቱን በመከተብ ምግብዎንና መጠጥዎን በጥንቃቄ መምረጥ አለብዎት፡፡

 

ወባ (MALARIA) 

ወባ በፓራሳይትና በበሽታው በተያዘ ትንኝ የሚከሰት ከባድ በሽታ ነው፡፡ ወባ በጣም ከባድ ህመም ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ለልጆችና ለአረገዙ ሴቶች አደገኛ ነው፡፡ እርሶ ወባ ባለባቸው ሀገሮች የሚጓዙ ከሆነ በበሽታው እንዳይያዙ የጤና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

 

የተጓዦች ተቅማጥ

የሚመገቡትን ምግብ መምረጥ እዳለቦት ሌላው ጥሩ ምክንያት 

ተጓዦች ወይም ጎብኚዎች በጉዞዋቸው ወቅት የተቅማጥ በሽታ በሚያጋጥማቸው ሰዓት ምክንያቱ ባክቲሪያ ወይም ቫይረስ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን አብዛኛው ጊዜ በባክቲሪያ ምክንያት ነው የሚመጣው፡፡ ባክቴሪያው በተጓዡ ሰውነት ውስጥ በተበከለ ውሃ ወይም ምግብ ምክንያት ይገባል፡፡ ስለዚህ በበሽታው ላለመያዝ ያልከረመ አዲስና ትኩስ ምግብ ይምረጡ፡፡ ምግብ፣ ውሃ፣ በረዶ፣ ፍራፍሬና ጭማቂ ከመንገድ ላይ አይግዙ፡፡ በተለይ ሳይበስሉ የሚበሉ አትክልቶች ለምሳሌ እንደ ሰላጣና የመሳሰሉት እንዲሁም ከባህር ውስጥ የሚገኙ ምግቦች በደንብ ካልበሰሉና በጥንቃቄ ከልተጠቀምናቸው አደገኛ ናቸው፡፡ ቢሆንም ተገቢውን ጥንቃቄ ቢወስዱም አንዳንዴ በተቅማጥ በሽታ ይያዘሉ፡፡ ስለሆነም ለተጓዦች ለተቅማጥ የሚሆን መዳኒትና ክትባት አለ፡፡ ግን  በጤና ባለሙያ የታዘዙ መሆን አለባቸው ምንያቱም መድሀኒቱ ለሁሉም ሰው ስለማይሆን፡፡

 

ጉዳትን መከላከል

በየአመቱ ብዙ ተጓዦች ጉብኝታቸው በጉዳት ምክንያት ይቋረጣል፡፡ ለማስፈራራት ሳይሆን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለማስገንዘብ ነው፡፡ ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦችን ይመልከቱ።

ኢንሹራንስዎ በቂ የሆነ የጉዞ ኢንሹራንስ እንደሚሸፍን ማወቅ፡

ወቅታዊ ማስጠንቀቂያዎችን መከታተል፡

የጎዳና እንስሳቶች በበሽታ የተለከፉ ሊሆኑ ስለሚችሉ መጠንቀቅ፡

ለተጓዦች የሞተር ሳይክል አደጋ ሊያጋጥም ስለሚችል ቀበቶዎን ማሰር፡

 በሞተር ሳይክል፣ በብስክሌትና በመሳሰሉ በሚጓዙ ሰዓት ጥንቃቄ ያድርጉ፡

በውሃ ውስጥ ስፖርት በሚሳተፉ ሰዓት ላይፍ ጃኬት ይልበሱ፡

ልጆች በውሃ ውስጥ ምንግጊዜም ረዳት ይኑራቸው፡

 

የፀሐይ ብርሀንን መከላከል

ከባድ የፀሐይ ብርሀን ሰውነትን ስለሚያቃጥል (sunburn) ያጋጠመውን ሰው ብትጠይቁ ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ እንቅፋት እንደሚሆን ይገልፅልዎታል፡፡ ከዚያም በላይ በቆዳና በአይን ላይ የረጅም ጊዜ ጉዳት ያስከትላል፡፡ ካለጊዜው ማርጀትና የቆዳ ካንሰር ይጠቀሳሉ፡፡ መርሳት የሌለብዎት ነገር በቀዝቃዛና ደመናማ በሆነ ቀንም በአሸዋ ነጸብራቅና የመሳሰሉት (sunburn) ምክንያቶች ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል፡፡

Sunburn ለማስቀረት ፀሐይ በሚበረታበት ሰዓት ወይም በቀትር አለመውጣት፤ ሰንእስክሪን በየጊዜው መቀባት በደንብ የሚሸፍን ልብስ መልበስና ኮፍያ ማድረግ፡፡

 

ውሃ ለጤናዎ አደገኛ ሊሆን ይችላል

በአሁኑ ሰዓት የመንገድ ላይ ህመምን ለማስቀረት የሚመገቡትን ምግብ መምረጥ እንዳለብዎት አውቀዋል፡፡ የሚጠጡትንም ውሃ እንደዚሁ፡፡ ምክንያቱም ብዙ ዓይነት የኢንፌክሺን በሽታ ያመጣል፡፡ እንዲህ ዓይነት በሽታ በባክቴሪያና በቫይረስ በተበከለ ውሃ ምክንያት ይመጣል፡፡ ስለሆነም ክትባት በhepatitis A ላለመያዝ ይረዳዎታል፤ ሆኖም ለሌላ ውሃ ወለድ መሽታዎች ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

አብዛኛው ጊዜ የተጓዦች ማረፍያ ቦታዎች ንፁህ (chlorinated) ውሃ የሊላቸው ንህናቸውም አናሳ ሲሆን የውሃ ደህንነትም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው፡፡ ስለሆነም ጥርስዎን በመታጠብዎ ብቻ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ውሃ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከል የሚከተሉትን ነጥቦች ይመልከቱ፡-

ንፁህ ብርጭቆ ወይም መጠጫ ከሌለ የታሸገውን ውሃ እንደዚሁ ከእቃው ላይ ይጠጡ፡

የታሸገ ውሃ ካልተገኘ ውሃውን አፍልተው ወይም የተበከለውን ውሃ የሚያፀዱ ኬሚካሎችን በመጠቀም ይጠጡ ፡

ሻይ ወይም ቡና ለመጠጣት በፈለጉ ሰዓት በፈላ ውሃ የተዘጋጀ ቢሆን ይመረጣል፡

ውሃ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ቢራና ወይን ለገበያ እንዲሆኑ ተደርጎ በንጽህና ስለሚዘጋጁ የታሸጉትን ይጠቀሙ፡

በረዶ ከተበከለ ውሃ የተሰራ ሊሆን እንደሚችል ማወቅም ብልህነት ነው፡፡

 

ጉዞ እና የግል ደህንነት

በሚያሳዝን ሁኔታ በብዙ ሀገሮች ስርቆትና ድብደባ እያደር እየባሰ የመጣ ችግር ሆኗል፡፡ ጎብኚዎች የዚህ ችግር ተጠቂዎች ናቸው፡፡ ስለሆም ሀገር ቤት ባሉ ሰዓት የሚያደረጉትን ጥንቃቄ በጉዞ ወቅትም ያድርጉ፡፡

በዙርያዎ ያሉትን ነገሮች በጥንቃቄ ይመልከቱ በተለይ የሚያጠራጥር ነገር ሲያዩ በንቃት ይከታተሉ

ካሜራዎን፣ ጌጣጌጥዎንና ሌሎች ውድ እቃዎችን ከእይታ ይሰውሩ፡

ርቀው አይሂዱ ፡ ሰው አልባ ወደሆኑ መዝናኛዎች አይሂዱ፡

ብቻዎን አይጓዙ በተለይ በመሸ ሰዓት፡

የትራፊክ መብራት በሚጠብቁ ሰዓት በንቃት ይሁን፡

የታጠቁ ዘራፊዎች የዝርፊያ ሙከራ ካደረጉቦት ለመከላከል ወይም ለመታገል እንዳይሞክሩ፡

ወታደራዊ ቦታዎችና ኢንዱስትሪዎችን ፎቶ እንዳያነሱ፡

ጠቃሚ የሆኑ ዶክሜቶችንና የባንክ  ካርዶችን ፎቶኮፒ ያድርጉና ሁሌ በሚይዙት ቦርሳ ሳይሆን በሌላ ቦታ ያስቀምጡት፡

 

ከመሄድዎ በፊት ይወቁ

ከመነሳትዎ በፊት ስለሚያርፉበት ቦት አስፈላጊውን መረጃ መሰበሰብ ለምሳሌ፡-

በሚያርፉበት ቦታ የባንክ ATM እና debit ካርዶች እንደሚሰሩ መጠየቅ፡፡ ምክንያቱም ከሀገርዎ ውጭ ሄደው ብር ከሌለዎት መጎብኘትና መዝናናት አይችሉም፡፡

በአንዳንድ ሀገሮች ጎብኚዎች በተለይ ሴቶች የአስተናጋጁን ሀገር ክብር ለመጠበቅ አግባብ ያለው ልብስ መልበስ አለባቸው፡፡

በተወሰኑ እንደ ሳውዲ አረብያ ያሉ ሀገሮች መጠጥ ተጠቃሚ መሆን በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

አስታውሱ አብዛኞቹ አገሮች በአደንዛዥ እጽ ማዘዋወር ላይ ያላቸው ቅጣት ከባድና ጥብቅ ነው፡፡

የእርስዎ ያልሆነ ሻንጣ፣ ፖስታና የመሳሰሉትን ይዘው አይጓዙ። ምንም ዓይነት ምክንያት ቢኖርዎትም፡፡

በጉዞ ላይ ከተዋወቁት ወይም ከማያውቁ ሰው ጋር ሆነው ኬላ አይሻገሩ (አይጓዙ) ምክንያቱም ያሰው ወንጀለኛ ከሆነ አብረው በመገኘትዎ ብቻ ይታሰራሉ፡፡

ታክሲ ውስጥ ከመሳፈርዎ በፊት ሹፌሩ ህጋዊ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡

ያሉበት ቦታ ነገሮች የሚፈጸሙት እንደራስዎ ሀገር  አይደለም። ለምሳሌ ፎቶ ለማንሳት ፍቃድ ሊያስፈልግዎት ይችላል፡፡

አንድ ህጻን ከአንድ ወላጅ ጋር ወይም ከአንድ አዋቂ  ጋር ጉዞ እያደረገ ከሆነ ለልጁ የተለየ የፍቅርም ሆነ የጫወታ ምልክት ማሳየት በሀገሩ ነውር ሊሆን ይችላል።(ቱፍታ በሃገራችን እደግ ከፍ በል የሚል የምርቃትና የፍቅር መግለጫ ሲሆን በሊላው ሀገር ፍርድ ቢት የሚገትር ወንጀል ነው)እርስዎም ልጅ ይዘው ከተጉዋዙ  ከወላጆቹ ወይም አሳዳጊዎቹ የተፃፈና ፊርማ ያለው የድጋፍ ደብዳቤ ይኑርዎት፡፡

 

ለመሄድ ዝግጅትዎን ጨርሰዋል

እርግጠኛ ለመሆን፡-

ለአራት ሳምንታት ጤና ጣቢያ በመሄድ ለጉዞ የሚሆን ክትትል ማድግዎን፡

ወቅታዊ የሆኑ ክትባቶችን

የወባ መዳኒቶችን (በተፈቀደው መጠን)፡

የጉዞ ዶክሜቶችን እንደ ፓስፖርትና መለያ ፎቶ፡

የጤናና የክትባት መረጃዎችን፡

የአደጋና የጤና ኢንሹራንስዎን

የአየር መንገድ፣ የሆቴልና የመኪና ኪራይ ዶክመቶች፡

በአደጋ ጊዜ ተጠሪ አድራሻዎች፡

የግል መዳኒቶችን፡

የፀረ ተቅማጥ መዳኒቶችን፡

የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ ሳጥን፡

ሳንእስክሪን።

የዝናብ ልብሶችና ኮፍያ፡

አማራጭ ልብሶች፡

ዲክሽነሪና የጉዞ መረጃ የያዘ መፅሀፍ፡

ካሜራ፡

የፀጉር መንከባከብያዎች፣ መዋብያዎች የግል መገለገያዎች፡

ከቦታው ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር የሚመጣጠን አዳብተር፡

የእጅ መብራት፡

 

በስተመጨረሻ

ከጉዞ ወደ ሀገር ቤት በሚመለሱ ሰዓት ከጓደኞችዎና ከቤተሰብዎ ጋር ስላሳለፉት ጥሩ ጊዜ መጫወትና ፎቶዎችን በማሳየት ያሳልፉታል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ስሜት ካልተሰማዎት ሌላም ነገር ይዘው መጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ህመሞች ለወራቶች ያህል ምልክታቸው ስለማይታይ፡፡ በተመለሱ በሳምንታት ውስጥ ህመም ከተሰማዎት በተለይ ትኩሳት፣ የማያቋርጥ ተቅማጥ ወይም ትውከት፣ የቆዳ ቀለም መለወጥ፣ የሽንት ችግር፣ የቆዳና የአባለዘር በሽታዎች ከታዩቦት በአፋጣኝ  ወደ ጤና ጣብያ ይሂዱ፡፡

ከሶስት ወር በላይ ከተጓዙና በተላላፊ በሽታ የተያዙ ከመሰልዎም በፍጥንት ወደ ህክምና ይሂዱ፡፡

ምንግዜም የጉዞ ወይም የጉብኝት እቅድዎን በግዜ ያውጡ፡

የመከላከያ ህክምናዎች ለሁሉም ሰው ተስማሚ አይደሉም አንዳንዶች መጥፎ ጎን ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም ከመጠቀምዎ በፊት የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Travel safety ጉብኝት (ጉዞ)