የስራ ቦታ ደህንነትና ጤንነት

Written by  Thursday, 19 March 2015 17:50
Rate this item
(0 votes)

 

የስራ ቦታ ደህንነትና ጤንነት

 

በተመቻቸና ጤናማ በሆነ የስራ ቦታ መስራት  የሁሉም ሰራተኛ መብት ፍላጎትና ግዲታም ነው፡፡ ስለሆነም ሁሉም ኣሰሪዎችና ሰራተኞች በተቻላቸው አቅም የተመቻቸና ጤናማ የሰራ ቦታ የመፍጠር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ሁሉም ሰራተኛ በግልም ሆነ በጋራ ከአሰሪዎቻቸው ጋር በመተባበር በስራ ቦታ ላይ  ጉዳቶችና ህመሞች እንዳይፈጠሩ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በተለይ አሰሪዎች የስራ ቦታን የተመቻቸና ጤናማ የማድረግ  ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ 

አሰሪዎች ለሚወስዱትም ለማይወስዱትም እርምጃ ተጠያቂ ናቸው፡፡ የአሰሪዎች ህጋዊ ደህንነትና ጤንነትን ጨምሮ፡፡

ራሳቸውንና ሌሎችንም ሊፈጠሩ ከሚችሉ የጤና ችግሮች መጠበቅና መንከባከብ አለባቸው

የስራ መርጃ መሳሪያዎች፣ ልብሶችና፣ እቃዎችን ማሟላት፡

ከጤና ኮሚቴዎች ጋር ወይም ኃላፊዎች ጋር በመተባበር መስራት፡

የስራ ቦታ ደህንነትንና ጤናን በተመለከተ ከሌሎች ጋር ተባብሮ መስራት፡፡ አሰሪዎች ወይም የኮንትራት ሰራተኞች  የህግ ደህንነትና የጤንነት ግዴታን በተመለከተ የሚሰራና የሚቆጣጠርላቸውን ሰው ይመድባሉ ወይም ይቀጥራሉ፡፡

እንደአስፈላጊነቱ በደህንነትና በጤና ላይ ችግር እንዳይደርስ ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ምንያቱም ከጥንቃቄ ጉድለት ጉዳቶች እንዳይፈጠሩ፡፡

እርግጠኛ ለመሆን ስራዎችን ደጋግሞ ማየት፣ ማቀናጀት፣ ማስተካከል በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞችና አሰሪዎችን ደህንነት መጠበቅ  ማረጋግጥ፡፡

በስራ ላይ ያለ ሰራተኛ በደህንነቱና በጤናው ያለውን ህጋዊ መብት ለሟሟላት አጥጋቢ ውጤት ያለው አሰራር መከተል፡፡

በግል ስራ የሚተዳደሩ ሰዎች ደህንነትና ጤናን ተሞርኩዞ የሚወስኑት ውሳኔ የራሳቸው ኃላፊነት ነው፡፡

ሰራተኞች በሚሰሩ ሰዓት በጤናም ሆነ በደህንነታቸው እንዲሁም በአካባቢው ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ አስፈላፊው ጥንቃቄ ማድረግ፡፡

የህንፃ ባለቤቶች ወይም መሬታቸውን ለስራ ቦታ የሚጠቀሙ ህጋዊ ደህንነትና የጤና ኃላፊነት አለባቸው ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጨምሮ

በእነሱ ስር ያለ መገልገያ በጤናም ሆነ በደህንነት ላይ ችግር እንያመጣ መጠንቀቅ

በመተባበር የስራ አካባቢውን ለደህንነትም ለጤናም ምቹ ማድረግ፡፡ የተጠቃሚዎች ደህንነትና ጤንነት ጨምሮ

የተገዙ እቃዎች፣ መሳሪያዎች፣ መለዋወጫዎች እና የመሳሰሉት በተሰራላቸው መግለጫ መሰረት መጠቀም

ከሌሎች ጋር በመተባበር የስራ ቦታ ደህንነትና የጤና ጉዳዩችን በተመለከተ መስራት

አሰሪዎች 20 እና ከዚያ በላይ ሰራቶኞች ካሏቸው የጤና ኮሚቴ ማቋቋም አለባቸው፡፡  

ከ10-19 ሰራተኞች ባሉበት ቦታ (ግንባታ የሚካሄድበት ቦታ) አሰሪዎች የጤና ተጠሪ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

20 እና ከዚያም በላይ ሰራተኞች ባሉበት የስራ ቦታ ከ90 ቀናት በላይ የሚቆይ የግንባታ ስራ ባለበት አካባቢ ኮንትራክተሩ የጤናና የደህንነት ኮሚቴ ማቋቋም አለበት።

የጤናና የደህንነት ኮሚቴዎችና ተጠሪዎች የህግ ኃላፊነት

ደህንነትና ጤናን በተመለከተ ለሰራተኞች ሀሳቦችን ማቅረብ

የሰራተኛው ደህንነትና ጤንነት በተመለከተ የሚፈጠሩ ችግሮችን መፍታት

ጤናንና ደህንነትን በተመለከተ የሚሰሩ ስራዎችንና ይህንን ተመርኩዘው የሚሰጡ ስልጠናዎችን እንዲሁም ትምህርቶችን ማሳደግ፡

በየጊዜው የሚደረግ(ተከታታይነት ያለው) የስራ ቦታ ቁጥጥር ማድረግ፡

ደህንነትና ጤንነትን  በሚመለከት የሚደረጉ ምርመራዎች ላይ መሳተፍ፡

ደህንነትና ጤንነትን በተመለከተ ከሌሎች ጋር በመተባበር መስራት።

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Workplace safety የስራ ቦታ ደህንነትና ጤንነት