ግላዊ ኃላፊነት

Written by  Sunday, 15 March 2015 17:47
Rate this item
(3 votes)

ግላዊ ኃላፊነት

 

 

‹‹ነቃፊዎ በራሳቸው ስብዕና የታሰሩ ናቸው››

 

በመጀመሪያው አንቀጽ እንደተረዳነው በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚፈጠሩ ሁለት ያጋደሉ አካሄዶች አሉ፡፡

አንደኛው የነቀፋ ልማድ ሲሆን ጥፋተኛው ማን እንደሆነ የማሳመን የራሱ የሆነ ተፅኖ አለው::

ሁለተኛው ደግሞ የክስ ልማድ ሲሆን አንድ ሰው ኃላፊነት በመውሰድ ክስ ማቅረብ ናቸው።

ሁለቱን ያጋደሉ አካሂዶች ከህይወት ልምድ የወረስናቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ምርጫ ግን አለን፡፡ ምርጫችን ነቃፊ መሆን ከሆነ እሱን ተከትለው የሚመጡ ችግሮችንም መጋፈጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኃላፊነትን በመውሰድ ለራስ መጠቀም ናቸው፡፡

ከልማዳዊ አካሄድ መላቀቅ ምን ያህል ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡ ምክንያቱም ጥፋቱን ወደ ሌላው ወገን እንዲያጋድል ስለሚያደርግ፡

                                                                           Image result for responsibility 

 

ለራስዎ ተፅዕኖ የመፍጠር ሃይል እንዳለዎት ማመን; የተሟላ የተግባር መሣሪያ በመያዝ ስራዎትን በአግባቡ 

ማድረግ ወይም መስራት እችላለሁ ብሎ ማመን፡

ጥፋተኝነትን አምነው በመቀበልዎ በሰዎች ላይ ያለዎትን ተአማኒነት እንዲጨምር ማድረግ;

ሰዎች እዲሰራላቸው ለሚፈልጉት ስራ ውጤት እንዲያገኙ ሲፈልጉ እርስዎን ይመርጣሉ፡

የበለጠ ደስታና እርካታን የሚፈጥርልዎት ሲሆን ደግሞ መጨናነቅን ይቀንሳል።

የመወሰን ሃላፊነትን መቀበል

 

ችሎታዎችን ግምት ውስጥ በመክተት ከኃላፊነት ጋር የሚመጣጠን ስዕል ይኑርዎት፡

የበለጠ ችሎታዎን ለማዳበር ራስን ማዘጋጀት;

የመርዳት ፍላጎትዎ ኃላፊነት እንዲወስድ ማድረግ ከቻሉገደብ የለሽ የመማር ፍላጎት አንዲኖርዎ ያደርጋል።

ሌሎችን መርዳት እንደ ግል ኃላፊነትዎ ይውሰዱት፡

ከሚያገኙት ጥቅም የበለጠ ኃላፊነት ይሰማዎት፡

ኃላፊነትን እንደ ሸክም ሳይሆን እንደስጦታ መቀበል፡

ችግሮችን ሳይሆን መፍትሄው ላይ ማተኮር፡

ፈታኝ የሆኑ ነገሮች ሲገጥምዎት የመጀመሪያ እርምጃዎ መሆን ያለበት ስርአት ባለው መልኩ ነገሩን መወጣት እንደሚችሉ ማሰብ

ለቅሬታ አቅራቢዎች በአግባቡ መልስ መስጠትን መማር;

ለምሳሌ፡- አንድ ሰው አልችልም ቢልዎት አመስግነው ለስራው ሌላ ሰው እንደሚፈልጉለት መግለፅ

ሌላ ሰው ፡- ለምን በዚህ ፍጥነት ይከናወናል ብለው አሰቡ ወይም በዚህ ፍጥነት ይከናወናል ብለው አይጠብቁ ቢልዎት ለሚቀጥለው  ጊዜ በዛ ሰው ችሎታ ላይ ያለዎትን ግምት ዝቅ እንደሚያደርጉ በዘዲ ማሳወቅ

ጠንከር ባለ መልኩም ቀጥተኛ መግባባት መፍጠር አንደሚቻል ማሳወቅ።

 

                                           Image result for responsibility

እንደ ሥራ አስኪያጅነትዎ ስልጣንና ኃላፊነትን በአንድ መለኪያ (ሚዛን) ይመልከቱ፡

.ስልጣንዎን ተጠቅመው ሐላፊነትዎን አንዳይዘነጉ መጠንቀቅ፡

ስልጣኑ ስራዎን ማስፈጸሚያ ሐይል ወይም ጉልበት መሆኑን መረዳት፡

አርስዎ ስልጣኑ የሰጠዎትን  ጉልበት ካልተጠቀሙበት ኣደራዎ አንደሚሽመደመድም መረዳት፡

ሁሉን በኣግባቡ በስርኣቱ ከፈጸሙ ፡ ሁሉም በተከፈተለት ቦይ ኮለል ብሎ ከተጉዋዘ ከአርስዎ በላይ ጥረቱ የሰመረለት ደስተኛ ማን ይኖራል።

ለምሳሊ አርስዎ የበታች ሰራተኛው ዘንድ በ ኣካል ተገኝተው ያለውን ኣሰራር፡ ኣመራር ፡ድክመትና ጥንካሪ ካላዩ ኣለቆች የሚያቀርቡልዎትን ሪፖርት ብቻ ተደግፈው የሚወስኑ ከሆነ  ይህ የስማ በለው ኣካሂድዎ አርስዎንም ድርጅትዎንም ለውድቀት ይዳርገዋል። ኣበው  አንዳየን አንፈርዳለን አንዳሉ።

ይህን ሲያደርጉ ደስተኛ፡  ሰላማዊ፡ ደህንነቱና አድገቱ የተጠበቀ  ሰራተኛ ይፈጥራሉ። አርስዎም ኣንቱ ተብለው ተከብረው በኩራት ይራመዳሉ።

በአርስዎ የኣመራር ብስለት ምክንያት ሊከሰት የነበረን ኣደጋ  ማስወገድ ወይም ሊጠፋ የነበረን የሰው ሕይወት ማትረፍ የመሰለን ከጸጸትና ከግዲለሽነት የጸዳ ኣአምሮ ይዞ መገኘት ምንኛ ታላቅ ድል ነው።

 

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Workplace safety ግላዊ ኃላፊነት