መንገድን በጋራ ስለመጠቀም

Written by  Thursday, 19 March 2015 17:56
Rate this item
(0 votes)

 

መንገድን በጋራ ስለመጠቀም

ረዥም አርቀት በሚያሽከረክሩ ሰዓት ብቻዎን ሲሆኑ አንዳንዴ በዓለም ላይ ከእርዎ በቀር ሌላ ሰው መኪና የሚያሽከረክር  ያለ መስሎ ላይሰማዎ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሊያስተውሉ የሚገባዎት ነገር መንገዱ ላይ እርስዎ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም በመቶዎች የሚቆጠሩ አሽከርካሪዎች እርስዎ በሚያሽከረክሩበት መንገድ እያሽከረከሩ እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እርስዎ በሚያሽከረክሩ ወቅት ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለብዎትና ሌሎች በመንገዱ ላይ የሚያሽከረክሩትንም እንዴት እንደሚያሽከረክሩ መከታተል ኣለብዎ ፡፡ ሁላችንም በጥንቃቄ እያሽከረከርን መንገዱን በጋራ መጠቀም ይኖርብናል፡፡

 

በተፈቀደው ፍጥነት ማሽከርከር

የትራፊክ መጨናነቅ ቢኖርም፣ የሰዓት መጣጠብ ቢገጥመንም ከተፈቀደልን ፍጥነት ውጪ ማሽከርከር የለብንም፡ ምክንያቱም የትራፊክ ምልክቶቹ የተቀመጡት ለምክንያት ስለሆነ፡፡ በፍጥነት ካሽከረከሩ ግን አንዳንዴ በትራፊክ ፓሊስ ይቀጣሉ ካልሆነ ግን ከሌላ መኪና ጋር ወይም ከእግረኛ ጋር አደጋ ሊያጋጥምዎት ይችላል፡፡

መንገድ በሚቀይሩ ሰዓት ጥንቃቄ ያድርጉ

በፍጥነት በሚያሽከረክሩ ሰዓት በመኪናዎች መሀል ቆርጦ ለመግባት አይሞክሩ፡ ምክንያቱም መኪናዎን በማረጋጋት ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው ካልገቡ ሌሎቹ አሽከርካሪዎች ምን ዓይነት እርምጃ ሊወስዱ እንደሆነ ስለማያውቁ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ።

ሌሎች አሽከርካሪዎችን አያበሳጩ

በአሁኑ ሰዓት እያሽከረከረ ያለ ሰው ለመበሳጨት ቅርብ ነው፡፡ እርስዎ ግን ከዚህ ይራቁ፡ ማንኛውም መኪና አሽከርካሪ ህገወጥ ነገር ሲያደርግ ቢያዩት እያንዳንዱን እንቅስቃሴውን ይከታተሉ እንጂ በመበሳጨት ለመጣላት አይሞክሩ፡፡ ይህ ክትትልዎ አራስዎን ከኣደጋ ሲያድንልዎ፡ ሊላ ተመሳሳይ ወንጀል አንዳይፈጸም ለመርዳትም ያግዛል።

ካለአግባብ (በህገወጥ) አያሽከርክሩ

ምንግዜም የራሳችንን ደህንነት በማስቀደም ማሽከርከር ቢኖርብንም በተጉዋዳኝ የሊላውንም ኣሽከርካሪ ደህንነት መጠበቅ ግዲታ ነው። ለሊላው ባለማሰብ በግዲለሽነት ካለአግባብ ማሽከርከር የለብንም። ይህም ማለት በፍጥነት አለማሽከርከር፣ ቀይ መብራት  በሚበራ ሰዓት ጥሶ አለመንዳት፣ በአደገኛ ሁኔታ ግራ ቀኝ ሳያዩ መኪናዎን በቀጥታ ኣለማሻገር፣ ሌሎች በሚያሽከረክሩበት ሰዓት አቋርጦ አለመግባት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ረፍዶብዎት ቢሆን እንኳን እነዚህን ሁሉ ህጎች ተላልፈው ባሰቡበት ሰዓት ሊደርሱ ቢሞክሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።ዛሪ ኣደጋውን ያመለጡት  ቢሆን አንኩዋን ለነገው ታጥበው ታጥነው የተዘጋጁ ነዎ።

መንገዶችን ከብስክሌቶች ጋር መጠቀም

በመንገድ ላይ ስንጓዝ ስለመኪኖች ብቻ አይደለም ማሰብ ያለብን ሞተር ሳይክል፣ ባጃጅ፣ ብስክሌቶችንም በጥንቃቄ መከታተል አለብን፡፡ የመንገዱ ሁሉ ተጠቃሚ ደህንነት እንዲጠበቅ የአርስዎ በመንገዱ ላይ በትኩረት ማሽከርከር ወሳኝ ነው ፡፡

ብስክሌቶችን በአግባቡ እንከታተል

የሚጠቀሙበት መንገድ ብስሌቶችንም እንዲጨምር ተደርጎ የተሰራ ከሆነ ምንግዜም ብስሌቶችን በጥንቃቄ ማየት አለብዎት ምክንያቱም ብስክሌት የሚነዱ ሰዎች ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው ለደህንነታቸው የሚሆን የአደጋ መከላከያ ኮፍያ ብቻ ነው የሚያደርጉት ፡ ያውም ካደርጉ። ስለሆነም አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ ጉዳቱ ከባድ ነው የሚሆነው ስለዚህ ከብስክሊቶች መራቅ ብልህነት ነው፡፡

የእጅ ምልክቶችን ማወቅ

ብስክሌት የሚነዱ ሰዎች ምልክት የሚሰጡ መበራቶች የሏቸውም ስለዚህ ለመጠምዘዝ በሚወስኑበት ጊዜ በእጃቸው ምልክት ይሰጣሉ ፡ ስለዚህ እነዚህን የእጅ ምልክቶች ማወቅ ያስፈልጋል። ያ ማለት ምን ማለት አንደፈለገ ፡ ወይም ወዲት መታጠፍ አንደፈለገ ለማወቅ መሞከር ፡ የኣጅ ምልክቱን መረዳት ካልቻልን በዝግታ የራሱን ውሳኒ አስኪፈጽም በዝግታ አያሽከረከሩ መጠበቅ መልካም ነው። 

ሞተር ሳይክሎች ችግር ላይ አይጥሉም

ብታምኑም ባታምኑም በሞተር ሳይክል ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎች በአሽከርካሪዎቻቸው ቸልተኝነት ምክንያት ነው፡፡ አብዛኞቹ  አሽከርካሪዎች ለብስክሌቶችም ሆነ ለመኪና ጥንቃቄ አያደርጉም በዚህ ምክንያት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በክረምትም ሆነ በበጋ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን በጥንቃቄ ሳያቁዋርጡ ይመልከቱ፡፡

ከእግረኞች ጋር መንገዶችን በጋራ መጠቀም

አብዛኞቹ መንገዶች ከእግረኞች ጋር በጋራ የምንጠቀምባቸው ናቸው፡፡ በመኪና መንገድ እግሮኞች ምንግጊዜም ቀኛቸውን ይዘው መጓዝ አለባቸው፡፡ በመኖሪያ አካባቢዎች እየነዱ ከሆነ ግን ምንጊዜም ጥንቃቄ ያድርጉ ብዙ ህፃናት፣ መንገድ የሚያቋርጡ ነዋሪዎች ስለሚኖሩ ጥንቃቄ በማድረግ ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት አለብዎት፡፡ እግረኞቹ ተሻግረው እስከሚጨርሱም ጠብቋቸው፡፡

አብዛኛውን ጊዜ እግረኞች በእግረኛ መንገድ ነው የሚጓዙት  ነገር ግን አንዳንዴ እግረኞች በመኪና መንገድ ይጓዛሉ፡ ስለሆነም እርስዎ ፍጥነትዎን በመቀነስ ለእግረኞች ቅድሚያ ይስጡ፡፡ ልብ ይበሉ በመኪናዎ ለሚያደርሱት ኣደጋ ወይም ግጭት ቀጥተኛ ተጠያቂው አርስዎ ነዎት። አርስዎ ጥፋተኛ ባይሆኑ አንኩዋን መጉላላትና የገንዘብ ብክነት ይደርስብዎታል።

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Road safety መንገድን በጋራ ስለመጠቀም