ኣምቡላንስ፡፡ የእሳት ኣደጋና የፖሊስ መኪና

Written by  Thursday, 19 March 2015 17:51
Rate this item
(1 Vote)

የመኪና አሽከርካሪዎች አንቡላንስንና የእሳት አደጋ መኪናዎችን አቁመው ማሳለፍ ኣለባቸው

 

ጥያቄ፡-  በማሽከረክርበት ሰዓት ከኋላዬ የእሳት አደጋ መኪና ወይም ኣምቡላንስ ወይም ደግሞ የፖሊስ መኪና የአደጋ ምልክት ቀይ መብራት እያበራና ድምጽ እያሰማ ቢመጣ ምን ማድረግ አለብኝ

 

መልስ፡- ዋናውን መንገድ በመልቀቅ ወደ ቀኝ መኪናዎን ካስጠጉ በኋላ መኪናዎን በመቆጣጠር እግርዎን ፍሬን ላይ ማስቀመጥ፡፡ ምክንያቱም ከኋላ የሚመጣው የእሳት አደጋ መኪና የመኪናውን የኋላ መብራ እንዲያየው። ከዚያም የድንገተኛ ኣደጋ መኪናው ሲያልፍ ጠብቆ በዝግታ መኪናን ኣስተካከሎ መሂድ ፡፡ነገር ግን የኣደጋ መኪናውን 500 ጫማ ያህል መራቅ ያስፈልጋል።

 

ጥያቄ፡- የእሳት አደጋው መኪና ከኋላዬ ሲመጣ እኔ ወደ ግራ እየተጠመዘዝኩ ቢሆንና በቀኜ ደግሞ መኪናዎች ቢኖሩስ ? 

 

መልስ፡- ኣለም ኣቀፍ ህጉ እንደሚለው መንገድ በመልቀቅ በቀስታ ወደ መኪና መስመር መግባት ከዛም ማቆም ነው፡፡ የህዝብ አደጋ መከላከያ መኪናው ሹፌር በየትኛው መንገድ እንደሚመቸው መርጦ በጥንቃቄ በግራ ወይም በቀኝ ያልፋል፡፡

 

ጥያቄ፡- የአደጋ መከላከያው መኪና በሚመጣበት ሰዓት በእግሬ እየተጉዋዝኩ ቢሆንና አረንጓዴ መብራት በርቶ ለመሻገር ተዘጋጅቼ ቢሆንስ?

 

መልስ፡- ለአደጋ መከላከያው መኪና መንገድ መልቀቅ ይኖርቦታል፡ ልክ መኪና ሲያሽከረክሩ እንደሚያደርጉት። የህዝብ ኣደጋ መከላከያ መኪናውን ለመተባበር እግረኛ ወይም ኣሽከርካሪ ኣይለይም። የእርስዎ መጣደፍ ሕይወትና ንብረትን ለማዳን ከሚቸኩል በላይ ኣይሆንምና።

 

ጥያቄ፡- መንገድ ላይ አደጋ በሚኖር ሰዓት የእሳት አደጋ መኪናዎች ለምንድነው አደጋ ያለበት ቦታና ቀጥሎ ያለውንም መስመር የሚዘጉት?

 

መልስ፡- መንገዶቹ የሚዘጉበት ምክንያት የአደጋ መከላከያ ሰራተኞችና የተጎጂዎች ደህንነትን ለመጠበቅ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ገጠመኝ በጣም አደገኛ በመሆኑ ም ጭምር ነው። ብዙ ጊዚ የአደጋ መከላከያ ሰራተኞች ጉዳተኞችን ለመርዳት በሚያደርጉት ጥረት የሞት አደጋ ጭምር ያጋጥማቸዋልና ነው፡፡

 

ጥያቄ፡- ኣነስተኛ(ጠባብ) መንገድ ላይ ቀኜን ይዤ  እየሄድኩ አምቡላንስ ድምጽ እያሰማ ቢመጣና ቢቆም ምን ማድረግ አለብኝ፡፡

 

መልስ፡- ወደ ግራ ራቅ ብለው ይጠጉና የቆመውን አንቡላንስ እንዲያልፍ ይንገሩት፡፡ መንገዱ ሶስት ወደ ተመሳሳይ አቅጣጫ የሚሄድ መስመር ካለው በጥንቃቄ በስተግራ ወዳለው መንገድ ኣስጠግተው ያቁሙ፡፡  

 

ጥያቄ፡- ከፊትለፊቴ የእሳት አደጋ መኪና የውሃ መርጫ ቱቦ ተዘርግቶ መንገድ ላይ ቢቆም ምን ማድረግ አለብኝ

 

መልስ፡- በቱቦው ላይ እንዳይነዱ ምክንያቱም የውሃውን ዝውውር ስለሚገታ። ቱቦው ላይ የሚሰሩትን የአደጋ

ተከላካይ ሰራተኞች ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል ህገወጥ አካሄድም ነው። ምሳሊም ከፈልጉ የእርስዎ መኪና ጎማ የውሀ ማስተላለፊያ ቱቦውን ሲረግጠው ውሀውን የሚገፋው ሞተር ከኣቅም በላይ የሆነ ግፊት ያጋጥመውና ሞተሩ እስከ መፈንዳት ሊደርስ ይችላል። ወይም ደሞ የእርስዎ መኪና ጎማ ልክ እንደለቀቀው የታፈነው ኣየርና ውሀ በሀይልና በጉልበት ተወርውሮ እስከ ሞት የሚያደርስ ኣደጋ ይፈጥራል። (ቪድዮ ይመልክቱ)   

 

ጥያቄ፡- እቤት ውስጥ ልጄ ጉዳት ቢደርስበትና እግሩ የተሰበረ መስሎኝ አንቡላንስ ብጠራ ልጄን የያዘውን አንቡላንስ እየተከተልኩ ሆስፒታል መሄድ እችላለው?

 

መልስ፡- አንቡላንሱ ድምጽ እያሰማና ቀይ መብራት እያበራ የሚሄድ ከሆነ ባይከተሉት ይመረጣል። አለበለዚያ ከ500 ጫማ ርቀት በላይ መጠጋት ኣይችሉም፡፡

 

ጥያቄ፡- የተማሪዎች ሰርቢስ ይዤ ተማሪዎችን እያወረድኩ የእሳት አደጋ መኪና ከኋላ ቢመጣብኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

መልስ፡- በጥንቃቄ ወደቀኘ አስጠግተው ያቁሙ፡፡ የኢትዮጵያ ህግ የሚለው ነገር ባይኖርም የአደጋ መከላከያው መኪና የተማሪዎቹን ሰርቪስ አልፎ አይሂድ፡፡ የተማሪዎቹ ሹፌር ተማሪዎቹ ሁሉ በሰላም መውረዳቸውን ሲያረጋግጥ ከዚያ የህዝብ ኣደጋ መከላከያ መኪናው ማለፍ ይችላል ።ወይም ተማሪዎቹን ገና ማውረድ ኣልጀመረ ከሆነ ቅድሚያውን ለኣደጋ ተከላካዩ መስጠት ይኖርበታል።

Last modified on Friday, 20 March 2015 04:48
Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Road safety ኣምቡላንስ፡፡ የእሳት ኣደጋና የፖሊስ መኪና