ጠጥቶ ማሽከርከር

Written by  Friday, 13 March 2015 01:23
Rate this item
(1 Vote)

የትራፊክ ፖሊስ ምንጭ እንደሚያሳየው አብዛኛው የሞት አደጋ የሚያጋጥመው ጠጥቶ ከማሽከርከር ጋር ያያዥነት ባላቸው አደጋዎች ነው፡፡ 10 ኢትዮጵያውያን 3 ከመጠጥ ጋር ተያያዥነት ያለው አደጋ ያጋጥማቸዋል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንን አደጋ የሚጋፈጡት ግን በአደጋ ልጆቻቸውን ያጡ ወላጆች፣ የትዳር አጋራቸውን ያጡ ባለትዳሮች፣ ልጆቻቸውን ያጡ ወላጆች፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች ናቸው፡፡          

ስለዚህ እርስዎ ይህንን ከመጠጥ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥመውን አደጋ ለመቀንስ ምን ለማድረግ አስበዋል 

መጠጥ በሚጠጡ ሰዓት 

ከመውጣትዎ በፊት መኪናዎን የሚነዳ ሹፌር ወይም መጠጥ የማይጠጣ ሰው ይምረጡ አለበለዚያ ታክሲ፣ አቶቢስ፣ ባቡር፣ባጃጅ እና የመሳሰሉት ጠጥቶ ከማሽከርከር ይልቅ መወሰድ ያለባቸው አማራጮች ናቸው፡፡  መጠጥ የጠጣ ሰው ቢያጋጥሞት መኪና እንዳያሽከረክር ይከልክሉት፡፡

የድግስ ዝግጅት በሚኖር ሰዓት   

ተጋባዡን ህብረተሰብ ለስላሳ መጠጥ እንዲጠቀም እንጂ አልኮል እንዲጠቀም አያስገድዱ፡፡ ባይሆን ተጋባዡን በደንብ እንዲመገብ መጋበዝ፡፡ ምክንያቱም ምግብ የአልኮልን ስርጭት ይቀንሰዋል፡፡ ስለሆነም የምግብ ፍላጎት የሚከፍቱ ምግቦችን መጋበዝ፡፡ ግብዣው ከማለቁ ቀደም ብሎ አልኮል መጠጦችን አለማቅረብ፡፡ ተጋባዦች አልኮል ጠጥተው ከሆነም አማራጭ መጓጓዣዎን እንዲጠቀሙ ማድረግ፡፡

 

ጠጥተው የሚያሽከረክሩትን መለየት 

 ህግ አስከባሪዎች እንደሚሉት ጠጥቶ ከማሽከርከር ጋር ተያያዥነት ያላቸው የትራፊክ ምልክቶች አሉ

·  በሰፊው ማዞር

·  እያንገጫገጩ መንዳት፣ አደባባይ ላይ በቀጥታ መንዳት

·  በተሳሳተ መንገድ መንዳት

·  ዝቅተኛ በሆነ ፍጥነት ማሽከርከር

·  ካለምክንያት ማቆም

·  ለተራፊክ ምልክቶች ቀሰስተኛ የሆነ ምላሽ መስጠት

·  በህገወጥ መልኩ መጠምዘዝ

·  በምሽት ጊዜ መብራት ሳያበሩ መንዳት       

እነዚህን ነገሮች በአእምሮአችን ከያዝናቸው ከአደጋ ማምለጥ እንችላለን፡፡ መኪና የሚያሽከረክር ሰው የጠጣ መስሎ ከታይዎት ከአጠገቡ ርቀው ለፓሊስ ያሳውቁ እንጂ እራስዎት ለማስቆም አይሞክሩ፡፡   

ጠጥቶ ማሽከርከር የታዳጊ ወጣቶች ችግር ነው?  

       

ታዳጊ ወጣቶች በተፈጥሮ ችኩሎች ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ የተከለከሉትን ነገር ማድረግ ይወዳሉ መኪና ማሽከርከርና  አልኮል መጠጣትን ጨምሮ፡፡   አልኮል መጠጣትና ማሽከርከር አንድ ላይ ሲጣመር የሞት አደጋን ያመጣል፡፡ ታዳጊዎች ደግሞ ለራሳቸው የተሻለ ውሳኔ እንደሚወስኑ ያምናሉ፡፡ ሁሉኑም ነገር በብቃ የሚወጡ ይመስላቸዋል፡፡  ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጠጥተው የሚያሽከረክሩ ታዳጊዎች ሳይጠጡ ከሚያሽከረክሩ ታዳጊ ወጣቶች 18  እጥፍ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው : በታዳጊ ወጣት ሴቶች ደግሞ 54 እጥፍ :

 

እርስዎ ጠጥቶ ከማሽከርከር ጋር የተያያዘ አጋጣሚ ቢያጋጥምዎት ምን ያደርጋሉ

 

አንድ ሰው ጠጥቶ ማሽከርከር ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡

o   ቢራ ከሌሎች አልኮል መጠጦች ያነሰ ኃይል የለውም

o   ጠጥቶ ማሽከርከር በህግ የተከለከለ ነው

o   ቀዝቃዛ ሻውር፣ ንፁህ አየርና፣ ትኩስ ቡና ከስካር አያላቅቁም ምክንያቱም ከስካር ነፃ  ለመሆን ጊዜ ይጠይቃል፡፡

o   ከመጠጥ በፊት ምግብ መመገብ የአልኮልን ፍጥነት ይቀንሳል እንጂ ከስካር ነፃ አያደርግም

o   ታዳጊዎች የመጠጥና የማሽከርከር ችሎታቸው አናሳ ነው

o   አዋቂዎች በማሽከርከርም ሆነ መጠጥ በመጠጣት ልምድ አላቸው

o   ከመጠን ያለፈ ግፊትና ተፅኖ መጥፎ ጎንም ጥሩ ጎንም አለው፡፡ በተፅኖ   ስር ሆኖ ማሽከርከር አደጋ አለው፡፡ በተጓዳኙም የሚያሽከረክረውን ሰው እንዳይጠጣ ግፊት ሲደረግ ግን  አሽከርካሪው ሊተገብረው ይገባል፡፡

 

የጓደኛዎንና የራስዎን ባህርይ ጠንቅቀው ይወቁ   

      

ጓደኛዎ አልኮል ጠጥቶ በሆንና ማሽከርከር ባይኖርበት እንዳያሽከርክር ይከልክሉት ምክንያቱም ራሱን  ጎድድቶ ሌላ ሰው ሊጎዳ ስለሚችል፡፡ የእርስዎ ጠንካራ ውሳኔ ግን በጓደኛዎ ህይወት ላይ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ እርስዎ ወይም ሌላ ከመጠጥ ነፃ የሆነ ሰው የጠጣውን ጓደኛዎን ወደ ቤቱ ማድረስ  ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ እቤትዎ ወስደው በማሳደር የጓደኛዎን ህይወት መታደግ ይችላሉ፡፡ በታክሲም መሄድ ካለበት እርስዎ ይክፈሉ ማንም ጓደኛ ጓደኛው ጠጥቶ እንዲያሽከረክር መፍቀድ የለበትም፡፡ በምንም መልኩ ቢሆን ተስፋ ባለመቁረጥ ጓደኛዎ በሰላም እንዲደርስ ማድረግ ይኖርቦታል፡፡ 

እንደዚህ ዓይነት ጓደኝነት የበለጠ ፍቅርና መቀራረብን ይፈጥራል፡፡    

 

ምን ጊዜም ጠጥቶ ከማሽከርከር ይቆጠቡ

 

1.   አልኮል ለመጠጣት የሚወጡ ከሆነ  መኪናዎን እቤትዎ ትተው ይውጡ  ምክንያቱም  አንድና ሁለት ተብሎ ነው ከመጠን የሚታለፈው ሆኖም አብዛኛው ህብረተሰብ መኪና እያለው ወደ ቤት በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት መሄድ ስለማይፈልግ ችግር ላይይወድቃል፡፡

 ሹፌር ማዘጋጀት

2. ከጓደኞችዎ ጋር መዝናናት ጥሩ ጎኑ ሾፌር በማዘጋጀት ጠጥቶ ማሽከከርን ያስቀራል፡፡ 

 

መጠጥ አይጠቀሙ

3.  ትንሽ ጠጥቶውም ቢሆን ካሽከረከሩ ህይወትዎን ትልቅ አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡ ስለዚህ ምንም ሳይጠጡ ማሽከርከር ይመረጣል ከስካር ያስለቅቃሉ ብለው የሚያስብዋቸውን መንገዶች አይመኑባቸው

4.  አምስት ሲኒ ቡና ስለጠጡና በቀዝቃዛ ውሃ ስለታጠቡ በደምዎ ውሰጥ በላው አልኮል ላይ  ምንም ዓይነት ለውጥ አያመጣም ምክንያቱም አልኮል ከደምዎ ሊወጣ የሚችለው ጊዜ  በመስጠት ብቻ ነው፡፡ 

ሰዓት ይጠብቁ

5.  አልኮል ከተጠቀሙ በኃላ ብዙ ሰዓት ቆይተው ያሽከርክሩ ከመጠን በላይ አልኮል ጠጥቶው ካደሩ የማሽከርከር ችሎታውን ይቀንስዋል፡፡ ስለዚህ ከስካር ነፃ እንዳልሆኑ ትንሽም ቢሆን  ከተጠራጠሩ አይንዱ   ከጠጡም ምግብ ሳይመገቡ አይጠጡ 

6. ምግብ ተመግቦ መጠጣ የአልኮልን የስርጭት ፍጥነት ስለሚቀንሰው በባዶ ሆድዎ አይጠጡ

    አስተውሉ

7.  ምንም ሲያደርጉ አስተውለው ያድርጉ ምንጊዜም ጠጥቶ ማሽከርከር የሚያደርሰውን አደጋ ያስታውሱ፡፡ ጠጥቶ ማሽከርከር የማሽከርከር ልምድዎን ይቀንሰዋል ከህግ አኳያ ከተያዙም ቅጣቱ ከባድ ነው፡፡

 

Last modified on Friday, 13 March 2015 09:39
Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Driving safety ጠጥቶ ማሽከርከር