ማንኛውም ሰዓት የባቡር ሰዓት ነው

Written by  Monday, 30 March 2015 06:13
Rate this item
(6 votes)

ኛውም ሰዓት የባቡር ሰዓት ነው

 

አብዛኞቹ ሹፌሮች የመሻገሪያ መንገድ ላይ ባሉ የባቡር መንገድ (ሀዲድ) ዝም ብለው ነው የሚያቋርጡት፡ ምክንያቱም ባቡር በዚያ ሲያልፍ አይተው ሰለማያውቁ ሊሆን ይችላል።ወይም ደሞ ባቡር በዚያ እንደሚያልፍ ቢያውቁም ዘንግተውት ሊሆን ይችላል፡፡የህዝብ ማመላለሻ ባቡሮች የጉዞ ሰሊዳ ኣላቸው፡ ነገር ግን ዕቃ ጫኝ ባቡሮች በግዜ ሰሌዳ ስለማይጓዙ በየትኛውም ሰዓት በማንኛውም ቦታና አቅጣጫ ሊገኙ ይችላሉ። መሻገሪያዎችን ጨምሮ፡፡ ስለሆነም መኪና ማሽከርከር በሚያዘወትሩባቸው መንገዶች ባቡር ሊመጣ እንደሚችል መጠበቅ አለብዎት፡፡

 

ባቡሮች አይጠመዘዙም

የባቡር መሃንዲሶች (አሽከርካሪዎች) ባቡሩ ሀዲድ ላይ መኪና ወይም ሰው ሲያዩ ባቡሩን መጠምዘዝ ወይም ማዞር አይችሉም፡ ወደሌላ አቅጣጫ ማዞሪያ መሪ የለውም፡፡ ባቡር ሀዲዱን ብቻ ተከትሎ ነው የሚሄደው፡፡ ስለሆነም መሃንዲሶች እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲገጥማቸው ያላቸው አማራጭ ጡሩምባ ማሰማትና የአደጋ ጊዜ ማርሽ መጠቀም ብቻ ነው፡፡ ኢንጅነሩ የአደጋ ጊዜ ማርሽ ሲጠቀም ባቡሩ ይቆማል ግን ብዙ መንገድ ሄዶ አደጋዎች ካጋጠሙ በኋላ ነው ሊቆም የሚችለው፡፡

 

ባቡሮች ቶሎ አይቆሙም

   ከ12 - 20 ሚሊዮን ፓውንድ በጫነ  ባቡር የአደጋ ጊዜ የሚሆነውን ፍሬን ስንጠቀም ለመቆም አንድ ማይል ያህል ይፈጅበታል፡፡ ይህ ማለት ለመቆም የሚፈጅበት ርቀት 18 የኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን ማለት ነው፡፡ ለምን ይህ ሁሉ ርቀት ይፈጅበታል? መሪው ላይ ፍሬኖች አሉ ግን ይህን ያህል ርቀት ከሄደ በኋላ ነው ባቡሩን ሊያስቆሙት የሚችሉት፡፡ ምን ጊዜም የቀኛችሁን መንገድ አትጠቀሙ ምክንያቱም የባቡሩ ኢንጂነር መንገድ ሊለቅላችሁ ስለማይችል፡፡

      {youtube}hCo5sy7LIek{/youtube}

 

ማስጠንቀቂያዎችን አትለፉ

አንድ አንድ መሻገሪያዎች በአውቶማቲክ ማስጠንቀቂያ መሳሪያ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ባቡር ሲመጣ መብራት ይበራል፣ ድምጽ ያሰማል እንደዚሁም በባቡር መሻገሪያው ላይ ያለው አውቶማቲክ በር (gate) ይዘጋል፡፡ እነዚህ ባቡር ሲመጣ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው፡፡ ሌሎች አብዛኞቹ መሻገሪያዎች ግን የአደጋ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ብቻ ነው ያሉዋቸው፡፡ ወደ ፊት ሂድ የሚለውንም ጨምሮ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በቢጫ ቀለም የተሳለ የክብ ቅርፅ ውስጥ በጥቁር ቀለም "X" እና "R-R" የሚል ፅሁፍ የመሻገሪያ መንገዱ ላይ ይሳላል፡፡ ከግማሽ በላይ የሆኑት ግጭቶች የሚያጋጥሙት አውቶማቲክ ምልክቶች ባላቸው የባቡር መሻገሪያዎች ነው፡፡ ምክንያቱም አብዘኞቹ አሽከርካሪዎች በመሻገሪያዎቹ አካባቢ ማሽከርከር ስለሚወዱ አለበለዚያም ቀይ መብራት እየበራ ባቡሩን እንቀድመዋለን የሚል ሃሳብ ስላላቸው ነው፡፡

 

የተሳሳተውን አመለካከት ለይተው ይወቁት

ባቡር ትልቅና ግዙፍ ሰለሆነ ሰዎች እንደሚያስቡት ፈጣን አይደለም፡፡ ማለትም 17 ጫማ ቁመትና 10 ጫማ ስፋት ስላለው ይህ ግዙፍነቱ የተሳሳተ አመለካከትን በሰዎች ላይ አሳድሯል፡፡ ቀጥ ባሉት የባቡር ሀዲዶች ላይ ባቡሩ ሲሄድ ሩቅ ያለ ይመስለናል፡፡ እንደዚህ በተሳሳተ መንገድ ስናስብ ደግሞ ባቡሩ የሚሄድበትን ፍጥነት ለመገመት ከባድ ነው፡፡ ስለሆነም ባቡሩ ሳናስበው መሻገሪያው ላይ ይደርሳል፡፡

 

ወደ ባቡር አትንዱ

25% ያህል ግጭቶች የሚያጋጥሙት በባቡር መስመር መሻገሪዎች እንደ ሆነ ያውቃሉ? ሰዎችስ ወደ ባቡር አካባቢ ይሮጣሉመልሱ አዎ ብዙ ጊዜ፤ ምክንያቱም መኪና አሽከርካሪው በተለያዩ ምክንያቶች በፍጥነት ያሽከረክራል ለምሳሌ፡- ጨለማ፣  ዝናባማ፣ ጭጋግ ወዘተ እንደዚህ ባሉ ሰዓቶች አሽከርካሪዎች በፍጥነት ይነዳሉ፡፡ ስለሆነም የባቡር መሻገርያው ጋር አደጋ ያጋጥማቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መኪና አሽከርካረው ሙዚቃ፣ ራድዮ ወይም ደግሞ ከተሳፋሪዎች ጋር ሞቅ ያለ ጨዋታ ከያዘ የባቡሩን ጡርንባ አይሰማውም፡፡ ሁል ጊዜ ልናስታውስ የሚገባን ነገር የማስጠንቀቂያ ጽሁፎችን ማንበብ፣ ነገሮችን መከታተልና ማዳመጥ እንዳለብን ነው፡፡

 

አለማለፍ፣ አለመቆም ወይም ቦታ አለመቀየር

አንድ አሽከርካሪ መኪናዎችን እያለፈ መጥቶ የባቡር መሻገሪያ ጋር ሲደርስ የግጭት አደጋ ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ምንያቱም መኪኖቹን እያለፈ በሚመጣ ሰዓት መኪኖቹን ማለፉን እንጂ የመንገዱን ነፃ መሆን አያይም፡፡ ቢታየው እንኳ በፍጥነት እያሽከረከረ ስለሆነ መኪናዋን ማቆም ይከብደዋል፡፡ ስለሆነም ለመሻገር ከመሞከርዎ በፊት ቅድሚያ የባቡር መሻገሪያው ነፃ መሆኑም ያረጋግጡ፡፡ ብዙ አሽከርካሪዎች መሻገሪያው ላይ በመኪኖች መኃል ይጣበቁና በባቡር ይገጫሉ፡ አንዳዴም የባቡሩን አመጣጥ ገምተው መኪናቸውን ማውጣት እንደማይችሉ ሲረዱ ከመኪናቸው ወጥተው መኪናቸው ብቻ ይገጫል፡፡

አብዛኞቹ የባቡር መሻገሪያዎች ብረቶቹ ከመንገድ( ከመሪት) ከፍ ያሉ ናቸው፡፡  በዚህ ከፍታ ቦታ ላይ ሲያሽከረክሩ መኪናዋን በጉልበት ለማሽከርከር ወይም ማርሽ ለመቀያየር ከሞከሩ መኪናዋ ሀዲዱ ላይ ልትቆም ትችላለች፡፡ ስለሆነም መኪናዎት ሀዲድ ላይ እንዳትቆም ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

   {youtube}fKJyh9uFLAY{/youtube}

ሃዲድ ላይ መዘግየት

መኪናዎ  መንገድ በሚጨናነቅ ጊዜ ሃዲድ ላይ ቢያዝና ባቡር ቢመጣብዎት በፍጥነት ራስዎንና ተሳፋሪዎችን ይዘው ይውጡ፡፡ ሌላ ዓይነት እቃ ለመያዝ አይሞክሩ፡፡ ምክንያቱም ህይወትዎን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ትልቅ ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ ከመኪናዎ ላይ ሮጠው በሚያመልጡ ሰዓት ማስታወስ ያለብዎት ነገር  ባቡሩ በሚመጣበት አቅጣጫ ሆኖ በየትኛውም አንግል ሊሆን ይችላል ከሀዲዱ ርቆ መሮጥና ባቡሩ መኪናውን በሚገጭበት ሰዓት መስታወቶችና ቁርጥራጭ ብረቶች ተወርውረው ወይም ተበታትነው ስለሚመጡ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች መሮጥ በሌለባቸው አቅጣጫ ስለሚሮጡ ከባድ መቁሰልና እስከ ሞት አደጋ ይደርስባቸዋል፡፡

መኪናዎ በመሻገሪያው ላይ ተይዞ ባቡር ባይመጣ እንኳ ተሳፋሪዎችንና እራስዎን ከመኪናው አውጥተው ከአደጋ ነፃ ወደ ሆነ ቦታ በመሄድ ለሚመለከተው አካል ወይም ለፖሊስ የመኪናዎን ሁኔታ ያሳውቁ፡፡ እነሱ ይሄንን ሁኔታ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃሉ ባቡሩ ከመምጣቱ በፊት ሁኔታው ታውቆ መንገድ የሚቀይርበት ወይም ከመድረሱ በፊት ለማስቆም ይሞክራሉ፡፡

 

ሁለተኛውን ባቡር ተጠንቀቁ

ከአንድ በላይ ሀዲድ ያለው የባቡር መሻገርያ ጋር ሲሆኑ ወዲያውኑ ለመሻገር አይሞክሩ ምክንያቱም አንደኛው ባቡር ካለፈ በኋላ በሌላኛው ሀዲድ ሁለተኛው ባቡር እየመጣ ሊሆን ስለሚችል፡፡ አንደኛው ባቡር ሲያልፍ ሌላኛው መምጣቱን ወይም እየመጣ መሆኑን ማወቅ አይቻልም፡ ምክንያቱም የፊተኛው ባቡር የኋለኛውን ስለሚደብቀው ነው፡፡ ከአንድ በላይ ሀዲዶች ባሉበት መሻገሪያዎች ብዙዎች ትእግስት ከማጣትና ከግንዛቤ ጉድለት የተነሳ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እርስዎ ግን ሁሌም ስንት ሀዲዶች እንዳሉ ማወቅ ይችላሉ፡፡ ነጭ X ምልክት በጥቁር የተፃፈ "Trainroad crossing" የሚል ያለበት፡- ምን ያህል ሀዲዶች እንዳሉ ስለሚገልፅ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የቀኝ መንገድ እንዳንጠቀም ይገልጽልናል፡፡

 

ትልቅ ስህተት

አብዛኛው ሰው ሃዲዶች የህዝብ ንብረቶች ናቸው ብለው ያስባሉ፡፡ ወደ መዝናኛ ስፍራ መሄጃ ወይም  ሃዲዱን እንደ መዝናኛ ስፍራ፣ የእስፖርት ማዘውተሪያ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ሃዲዶችን የመጠቀም መብት ያላቸው ይመስላቸዋል፡፡ ሆኖም እውነታው ግን ሃዲዱ ላይ መሆን ወይም መታየት ያለባቸው ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ብዙዎች በሀዲድ ላይ በመሆን ህይወታቸውን አጥተዋልና፡፡

 

በድልድዮችና በዋሻዎች ላይ ጥንቃቄ አድርጉ

የባቡር መንገድ ያለባቸው ድልዮች ባቡር በማይኖርበት ሰዓት አደገኛ ቦታ አይመስለንም፡፡ በተረጋጋ መንፈስ እዛ ቦታ ላይ መገኘት ሊያስደስት ይችላል።በደንብ ይወቁ እዝያ ቦታ መገኘት ህገወጥ ከመሆኑም በላይ በማንኛውም ሰዓት ባቡር ሊመጣ ይችላል፡፡ በዚህ ሰዓት ሁለት ምርጫ ነው ያለው፡፡ እነሱም መዝለል ወይም መገጨት፡፡ የእግረኞች መንገድ ስለሌለ መሮጥም አይቻልም፡፡

ዋሻ ውስጥ ያሉ ሀዲዶች የድልድዮች አይነት አደጋ ነው ያላቸው የእግረኛ መንገድ ስለሌለው ሮጦ ማምለጥም አይቻልም፡፡ ባቡሩ ሲመጣ በባቡሩና በዋሻው ግድግዳ መካከል ያለው ክፍተት 14 ኢንች ነው፡፡ ስለሆነም አንድ ሰው በዛች ክፍተት መካከል ቆሞ ማምለጥ አይችልም፡፡

  

እግረኞች ጥንቃቂ እናድርግ

ሃዲዶች በሯጮች፣ የእግር ጉዞ በሚያደርጉ፣ የቤት እንስሳቶቻቸውን በሚያናፍሱና በመሳሰሉት ይዘወተራል፡፡ እዚህ ላይ አደጋው፡- ሁሉም ሰዎች በራሳቸው እንቅስቃሴ ስለሚጠመዱ ነው፡፡ ለምሳሌ አብዛኞቹ ሯጮች በheadphones ሙዚቃ እያዳመጡ ስለሚሮጡ የባበሩን ጡርንባ አይሰሙትም፡፡ የሚሰሙትም አደጋውን ማምለጥ ይሳናቸዋል፡፡ አብዛኞቹ ሰዎች ደግሞ በተሳሳተ መልኩ ባቡሩ ለእነሱ የሚቆም ይመስላቸዋል። አለበለዚያም ከኋላቸው የሚመጣው ባቡር ሌላኛው ሀዲድ ላይ ያለ ይመስላቸዋል፡፡

ሊላው እርስዎ በፍጥነት እያሽከረከሩ ባቡሩም ደርሶ መጋጨትዎ እርግጥ ከሆነና ጥቂት የማሰቢያ እድሉ ካለዎ (ካጋጠመዎ) የመኪናዎን መሪ ባቡሩ ወደሚሂድበት አቅጣጫ በፍጥነት ያዙሩ ፡ 

ይህ ዘዲ ከሰራልዎ ጥቂት የመዳን ተስፋ ይኖርዎታል። ወይም ፊት ለፊት ከሚደርሰው አደጋ ይልቅ በጎን የሚደርሰው አደጋ ቀለል ያለ ነው። (ይህን ቪድዮ ይመልከቱ)  {youtube}wm0ywsD9V88{/youtube}

ቀላል ክንውን ኣይደለም፡ የእርስዎ መኪና በፍጥነት ተጉዞ ፊት ለፊት ከባቡሩ ጋር ቢላተም ከመኪናዎ ሞተር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ሊወድም ጉዳትም ሞትም ሊያጋጥም ይችላል።

ይህ ዘዲ የመኪናዎን አንድ ጎን ብቻ በማስመታት የሚከናወን ይሆናል፡ እንግዲህ ይሂም ከተቻለ ነው። ከተቻለ ማለቲ ብዙውን ጊዚ ኣደጋ የሚከሰተው ነገሮች ከቁጥጥራችን ውጭ ሲሆኑ፡  

ለመዳን ምንም እንጥፍጣፊ እድል ሲታጣ ; መደምደሚያው ይሂ ነው ወደማይባለው ፡  ነገር ግን እጣ ፈንታችን እድል ተርታችን የወሰነልንን አሚን ብሎ ለመቀበል ስናመራ ማለት ነው።

በዚህን ወቅት ማይክሮ ሰኮንድም ብትሆን ጊዚዋ ካለች ትረዳልች፡ ስለዚህ ነው የአደጋ መከላከል(difensive drive) መምህራን በተቻለ መጠን ኣደጋው ከባቡሩ ጎን ለጎን እንዲሆን የሚመክሩት።

የፊት ለፊት የባቡር ኣደጋ ሊላው ክፋቱ ከመኪናው ጋር በሚላተምበት ወቅት በሚፈጠረው ግፊት የመኪናው ኣካል በባቡሩ ሃዲድ ውስጥ ገብቶ ብረቱን በማጣመም ወይም በመስበር ኣቅጣጫውንም በማስቀየርና ከመስመሩ በማስወጣት በተሳፋሪም ሆነ በንብረት ላይ አደጋ ማስከተሉ ነው።

ከዚህ ሁሉ ግን ፍጥነትን ቀንሶ መጉዋዝ ና የባቡር ትራፊክ ደህንነት ምልክቶችን በአግባቡ መተግበሩ ብልህነት ነው። 

ስለዚህ ሁሊም እናስብ በፍጹም በባቡር ሃዲድ ላይ ባለመጉዋዝና በአጠቃላይም ባለመቅረብ።  የባቡር  ሃዲድ  በምናቁዋርጥበት ጊዚ በፍጥነት በማለፍና ቦታውን ቶሎ በመልቀቅ ከመሻገራችን በፊት ባቡሩ ኣለመምጣቱን በማረጋገጥ።

ይህን ከፈጸምን  ባቡሩ መንገዱን ይዞ ይሂዳል እንጂ  ኣደጋ ለማድረስ ወደኛ ኣይመጣም።

 

Last modified on Wednesday, 11 November 2015 04:09
Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home